Addis Ababa 40/60 housing registration is scheduled to be conducted from August 12-23, 2013 at 116 Commercial Bank of Ethiopia Branches.
For those who live abroad (Diaspora), an office is prepared for registration at Bole sub city in front of Woreda 5 police station.
የ40/ 60 የጋራ መኖሪያ ቤት ምዝገባ ነሃሴ 6 በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 116 የባንኩ ቅርንጫፎችና በአንድ ልዩ ምዝገባ ጣቢያ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡
የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ምዝገባ ከነሃሴ 6/2005 ዓ.ም እንደሚጀመር ባንኩ ዛሬ ነሀሴ 4/2005ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል፡፡
ተመዝጋቢዎች ከሁለት አመት በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆነው የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉና ከዚህ ቀደም በሌላ የቤት ፕሮግራሞች ያልተመዘገቡ ሊሆንእንደሚገባምተገልጿል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምዝገባ ከሃምሌ 6-17/2005ዓ.ም ድረስ በቦሌ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ውስጥ በተዘጋጀው ልዩ የምዝገባ ጣቢያ ይከናወናል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታደሰ ፓስፖርትና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በአካል መገኘት የማይችሉት ደግሞ በውክልና ማስረጃ በተረጋገጠ ወኪል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መቆጠብ የሚችሉት ኢትዮዽያ በምትገበያይባቸው የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ መሆን እንዳለትም የባንኩ ም/ፕሬዘዳንት አቶ የኋላ ገሰሰ ገልፀዋል፡፡
በ40/60 የቤት ፕሮግራም ተጠቃሚ የቤቱን 40 በመቶ መቆጠቡን በማረጋገጥ ቀሪውንና 60 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከባንክ በሚያገኘው ብድር አማካኝነት የቤት ባለቤት እንደሚሆንም ተመልክቷል።
ፕሮግራሙ የመንግስት ቋሚ ሰራተኞች ሆነውበከተማው በሚገኙ በማናቸውም ተቋማት፣ በፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ልማት ድርጅቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቢሮዎች የሚሰሩ ሆነው በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩትንም ያጠቃልላል።
ከነሃሴ 6 እስከ 17/ 2005 ለሚካሄደው የምዝገባ መርሀ ግብር፣ ባንኩ ካለፈው ከ10/90 እና 20/80 ልምድ በመቀመር አዲስ አሰራር በመዘርጋቱ ለተሳታፊዎች ቀድሞ ቅጾች እንዲደርሱ ይደረጋል፤ ለዚህም ሲባል ከ8 መቶ ሺህ በላይ ቅጾች መዘጋጀታቸውን ነው የባንኩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ የኋላ ገሰሰ የገለጹት።
በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ለመመዝገብም ለአንድ መኝታ 1 ሺህ 33 ብር የቁጠባ ደብተሩ ሲከፈት የሚከፈል ሲሆን፣ ከዚያ በላይ እከፍላለለሁ የሚል ደንበኛም መክፈል ይችላል ተብሏል፡፡ ባለ ሁለት መኝታ ቤት እንዲሁ 1 ሺህ 575 ብር፣ ባለሶስት መኝታ 2 ሺህ 453 ብር ለመጀመሪያ ወር መቆጠብ ግድ ይላል።
በተጨማሪም ይህ ቁጠባን መሰረት ያደረገ የ60/40 የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ ሰንጋተራና ሳሪስ አካባቢ በሚገኙ ሳይቶች የተጀመረ ሲሆን እስካሁንም ከ20 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሀላፊ አቶ ክንዴ ብዙነህ ገልፀዋል፡፡
Source: ERTA
በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት እየተከናወነ የሚገኘው ምዝገባ ቆሞ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚሲዮኖች አማካኝነት የሚደረገው ምዝገባ በተመሳሳይ የጊዜ ሰሌዳ ከጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ እንዲሆን ተወስኗል።
I need more information about this please
Yes I want regester but how?